05/08/2025
ይሁኔ በላይን ከዚህ ቀደም የምናውቀው በዝነኛ ባህላዊ ዘፈኖቹ ነው፤ አሁን ደግሞ ሌላኛውን ገጹን ሊያሳየን እነሆ ‹‹ፍኖተ ጥበብ›› በሚል ርእስ ያዘጋጀውን ግለታሪኩን ሊያስነብበን ቀን ቆርጧል፤ በታሪኩ ውስጥ መውጣት መውረድን፣ ዐቀበት ቁልቁለቱን፣ ጭልጥ ካለው ገጠር የዓለም ቁንጮ እስከ ሆነችው አሜሪካ የተጓዘባቸውን መንገዶች እናያለን፡፡ ማየት ብቻ ሳይሆን አብረነው እንድንጓዝ የሚያደርግ መግነጢሳዊ ኃይል ያለው አስደናቂ መጽሐፍ ነው፡፡
‹‹ፍኖተ ጥበብ›› እውነተኛ የገጠር ሕይወትን፣ ባህል እና እምነትን፣ መልክዓምድራዊ ውበትን፣ ጥላቻና ፍቅርን፣ ደስታና ኀዘንን፣ ፖለቲካና ማኅበራዊ ሕይወትን ከሁሉም በላይ የአገር ቤቱን ጥበባዊ ሕይወት ፍንትው አርጎ ያሳየናል፡፡
በትክክለኛው የግለታሪክ አጻጻፍ ጥበብ የተዘጋጀው ፍኖተ ጥበብ መጽሐፍን አንዴ ከጀመርነው ማቋረጥ ይከብደናል፤ ስሜትን ሰቅዞ የመያዝ ዐቅም ያለው እጅግ ተነባቢ መጽሐፍ ነው፡፡ በመሆኑም ይህንን ድንቅ መጽሐፍ ስናነብ የይሁኔን ሌላ ገጽ ማየት እንችላለን፡፡ አይተንም ‹‹ወቼ ጉድ!›› ብለን በአድናቆት እንመሰጣለን፡፡
ብራቮ ይሁኔ!