31/05/2026
በዘንድሮው የ1447 ዓ.ሒ (2018 ዓ.ም) የሐጅ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተሳተፉ የኢትዮጵያ ሁጃጆች የሐጅ ስነ-ሥርዓታቸውን በስኬት አጠናቀቁ።
(ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም፤ ጄዳ) የዘንድሮው የሐጅ መርሃ-ግብር በስኬት መጠናቀቁን አስመልክቶ በጄዳ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስል ጀነራል ክቡር አምባሳደር ጣፋ ቱሉ እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር ሼህ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ በተገኙበት ውይይት የተካሄደ ሲሆን፤ ለዚህ ታላቅ ስኬት የበኩላቸውን ከፍተኛ አስተዋጽዖ ላበረከቱ አካላት በሙሉ በጋራ ምስጋና አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ሁጃጆችን በጊዜ በመመዝገብ፣ መረጃዎችን በተደራጀ መልኩ ተደራሽ በማድረግ፣ በጤና አጠባበቅና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ባሳየው የላቀ አፈፃፀም ከሳዑዲ አረቢያ የሀጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር ከፍተኛውን የአልማዝ (Diamond) ሽልማት በዘንድሮው የሐጅ ማጠናቀቂያ መርሃ-ግብር ላይ ማሸነፉ የሚታወስ ነው።
ክቡር ሼህ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ በሳዑዲ አረቢያ የነበራቸውን ይፋዊ የሥራና የሐጅ መርሃ-ግብር አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።