01/08/2026
ሀላባ ከነማ ሴኔጋላዊውን የተከላካይ አማካይ በዛሬው ዕለት የግሉ አድርጓል።
ለ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በጠንካራው ለመቅረብ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው ሀላባ ከነማ ሴኒጋላዊውን ሴክ ሳምባን ለማስፈረም ተስማምቷል
ሴክ በሲኔጋል ሊግ ለUS ouakam ከ2022 ጀምሮ በቋሚነት ቡድኑን ሲያገለግል የነበረና ባሳለፍነው የውድድር አመት በ26 ጨዋታዎች በቋሚነት በመሰለፍ 2,100 ደቂቃዎችን መጫወት የቻለ በcenteral midfielder እንዲሁም defensive midfielder ሆኖ መጫወት የሚችል ተጫዋች መሆኑን የተጫዋቹ ስታትስቲክስ ያሳያል።