05/07/2025
ፒኤስጂ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ደረሰ
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ፒኤስጂ አርሴናልን በድምር ውጤት 3 ለ 1 አሸንፎ ለፍፃሜው ደርሷል።
በመጀመሪያው ጨዋታ አርሴናልን በሜዳው 1 ለ 0 ያሸነፈው ፒኤስጂ ዛሬ ምሽት በሜዳው በተካሄደው ጨዋታም 2 ለ 1 አሸንፏል።
የዛሬውን የፒኤስጂ የማሸነፊያ ግቦች ፋቢያን ሩዪዝ ፔና በ27ኛው ዲቀቃ እና አሽራፍ ሐኪሚ በ72ኛው ደቃቂ ላይ አስቆጥረዋል።
አርሴናልን ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ ቡካዩ ሳካ በ76ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።
ጨዋታውን በድምር ውጤት 3 ለ 1 ያሸነፈው ፒኤስጂ ትናንት ባርሴሎናን በማሸነፍ ለፍፃሜው ካለፈው ኢንተር ሚላን ጋር ለዋንጫ የሚጫወት ይሆናል።