07/12/2025
Update
……..///…….
ከሰበታ ቁጥር 1 የኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ ወደ ጥቁር አንበሳ ኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ፤ ከጥቁር አንበሳ ኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ ወደ አዲስ ዌስት ወይም ኮልፌ ማከፋፈያ ጣቢያ በተዘረጋዉ 132 ኪ.ቮ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ መደበኛ የጥገና ሥራ ሲከናወን ውሏል፡፡
ይሁንና ጥገናው ተጠናቆ መስመር በሚሞከርበት ጊዜ በተፈጠረ የመስመሮች መነካካት በአዲስ አበባ እና በተወሰኑ የክልል ከተሞች የኃይል አቅርቦት ተቋርጧል፡፡
የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ርብርብ እየተደረገ በመሆኑ መስመር በተቋረጠባቸው አካባቢዎች የምትገኙ ደንበኞቻችን በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን፡፡
Ethiopian Electric Utility -የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት