27/01/2026
ፈጥኖ ደራሹ ጤና መድህን !
ህይዎት መልከ ብዙ ናት፡፡ የሰው ልጅ በህይዎት ውጣ ውረድ ውስጥ ብዙ አይነት ፈተናዎች ይገጥሙታል፡፡ ህይዎቱንም ለማስተካከልና የተሻለ ኑሮ ለመኖር መውደቅ ፣መነሳት ማግኘትና ማጣት ይጋረጡበታል፡፡
የሀገሬው ብሂል እንደሚተርተውም ‹‹ ጎኔን ከምድር አይኔን ከማገር አታውለው›› እንዲሉ አበው ለሰው ልጅ የተሟላ ጤና እጅግ መሳኝ ነው፡፡ ነገር ግን ባያጋጣሚ ጤናችን ቢታዎክ ደግሞ በጤና መድህን መታከምና መፈወስ ይቻላል፡፡
ጤና መድህን ትርፍን መሰረት ያላደረገ፣ ለዜጎች የጤና ዋስትና የሚሰጥ ነው፡፡ የጤና መድህን አባል ለመሆን አሰቀድመን በከፈልነው አነሰተኛ የገንዘብ መዋጮ መሰረት የጤና እክል የገጠማቸውን ግለሰብ ወይም ቤተሰብ ለህክምና የሚያወጡትን ወጭ በመቀነስ በተቋቋመው የጤና ፈንድ አማካኝነት ወጭን በመጋራት እንደ አቅም ማውጣት እንደ ህመማችን መታከም የሚያስችል የኑሮ ምርኩዝ ነው፡፡
ጤና መድህን ካሉት ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች መካከል በማህበረሰቡ መካከል የጋራ መስተጋብርን መፍጠር መቻሉ ነው፡፡ ህክምና ባስፈለገ ጊዜ ከልመና ወይም ከእርዳታ ነፃ ያወጣናል፣ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች ፈጥኖ ደራሽም ነው፡፡
ዜጎች ጤናማ በሆኑበት ወቅት የጤና መድህን ተጠቃሚ ከሆኑ የጤና ችግር ቢገጥማቸው ከስጋት ነፃ በመሆን ቀድመው በከፈሉት ተመጣጣኝ ክፍያ የተሸለ የጤና ህክምናዎችን በማግኘት እራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ማሳከም ይችላሉ፡፡
በሀገራችን የጤና መድህን ለመተግበር በ1986 ዓ.ም የወጣ የጤና መረጃ ያመላክታሉ፡፡ አንድ የጤና መድህን አባል ወይም ተጠቃሚ ለመሆን በሚያገኘው ገቢ ልክ ክፍያ ይፈፅማል፡፡ በዚህም መሰረት ሶስት የጤና መድህን አይነቶች አሉ፡፡
የመጀመሪያው ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ሲሆን ይህ መድህን በአነስተኛ ገቢ የሚተዳደሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የገጠሩን የማህበረሰብ ክፍልን የሚሸፍንና ሰፊውን ክፍል ይዞ ተደራሽ የሚያደርግ ነው፡፡
ሁለተኛው የመድህን አይነት ማህበራዊ ጤና መድህን ነው፡፡ ይህ በአብዛኛው ጊዜ በተለይ በመንግስት ሠራተኞችና በጡረተኞች ዘንድ የጤና ወጪ የሚጋራ ሲሆን 25 በመቶ የሆነውን የማህበረሰብ ክፍል ይሸፍናል፡፡ ሶስተኛው ደግሞ የግል የጤና መድህን ነው፡፡ ይህ በግል ደረጃ ግለሰቦች የጤና ኢንሹራንስ ወይም መድህን የሚገቡበት ስርዓት ሲሆን ብዙ ጊዜ ለትርፍ የተቋቋመ የጤና መድህን አይነት ነው።
የጤና መድህን ተጠቃሚዎች የጤና እክል ሲገጥማቸው ውል ከወሰዱ የጤና ተቋማት ላይ ያለ ገደብ የፈለጉትን ህክምና ይታከማል፡፡ ያለ ተጨማሪ ወጭ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ክልል ጤና መረጃ እንደሚያመለክተው ባሳለፍነው ዓመት በጤና መድህን ከ17 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ አደርጓል፡፡ መንግስትም የተጠቃሚውን አገልግሎት የበለጠ ለማሳለጥ በመንግስት ድርጅቶች፣ የእርዳታ ድርጅቶች እንዲሁም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ሀብት ያሰባስባል፡፡
የመድሃኒት አቅርቦት እጥረትን ለመፍታት በሀገር ውስጥ እንዲመረት ለፋብሪካዎች ግንባታ ድጎማ እያደረገ ነው፡፡ ይህም የጤና መድህን ያመጣው ትሩፋት ነው፡፡
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያሉ ዜጎችን ታሳቢ ያደረገ የህክምና አገልግሎት የሚሰጥበት አሰራር በመዘርጋት ጤናማና ደስተኛ ዜጋ ማብዛት የብልፅግና ፓርቲ ትኩረት ነው፡፡
ይህን ለማሳካትና የጤና መድህን ሽፋን በመላ ሀገራችን እንዲዳረስ አሰራርን በማዘመን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ደረጃውን የጠበቀ የጤና መድህን ሽፋን ተጠቃሚ እንዲሆን እየተሰራ ነው፡፡
~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/